Welcome To The Amhara Association of Bay Area


Opening


The Amhara people experience structural violence, discrimination, and marginalization. Amharas in Ethiopia are suffering from several forms of social and economic marginalization, including a lack of infrastructure, food, water, sanitation, and access to healthcare services. Furthermore, Amharas lack meaningful representation in both local and federal government, rendering them politically powerless. As a result of this deliberate marginalization, Amharas are the victims of ethnic cleansing, forced displacement, and genocide. Therefore, we acknowledge the necessity of peacefully organizing and working to oppose the oppressive system, ensuring Amharas achieve social and political justice, economic equality, and reclaim forcibly and unlawfully acquired territories.


To support the Amhara people’s fight for survival and freedom, we founded the Amhara Association of the Bay Area. Regardless of region, gender, or religion, all persons of Amhara heritage must struggle to achieve long-lasting societal change in order to address the complex, systemic issues Amharas face. This organization has no affiliation with or influence by Ethiopia's current ruling Prosperity Party, Amhara Prosperity, or any other political organization. On June 17, 2023, we thus established the Amhara Association of Bay Area, which will be administered by reputable Amharas that the association's members have chosen, with the support of Amharas in the Bay Area.



AABA's Vision 


The association's objective and vision are to be a dependable and trustworthy institution that addresses the economic, social and existential challenges facing the Amhara people and offers long-term, sustainable relief and solutions to improve Amhara’s general welfare. 


AABA's Mission 



AABA's Purpose 




Contact Us:


1319 Washington Avenue Unit 551, 

San Leandro, CA 94577 

amharabayarea@gmail.com

510-560-4215 




TwitterLinkInstagramFacebook

መግቢያ 


የአማራ ህዝብ መዋቅራዊ በሆነ ግፍ እና አይን ያወጣ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሀገራችን በኢትዮጵያ  እየተፈጸመበት ይገኛል። በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው የአምሓራ ህዝብ የምግብ ዋስትና የሌለው፤  በንጹህ  የመጠጥ ውሃ እጥረት  የሚሰቃይ ፤  የመሠረታዊ  ትምህርት  ተደራሽነት የሌለው ሲሆን፤ ለከፍተኛ ድህነት ፤ ለጦርነት እና ለእርስ በርስ ግጭት ፤  በሀገር ውስጥ መፈናቀል እና ለውጭ ሀገር ስደት ተዳርጓል። እንዲሁም  የመምረጥ እና የመመረጥ መብቶቹን በመግፈፍ፤ ሆን ተብሎ ከስልጣን እንዲገለል በማድረግ፤ ፍትሃዊ የሃብትና የንብረት ባለቤት እንዳይሆን በተደራጀና በተጠና መዋቅር ሲሰራበት ቆይቷል።  ባጠቃላይ የአማራ ሀዝብ በተደጋጋሚ ጦርነት ኢኮኖሚው እንዲወድም ተደርጎበታል።  ይህ የአምባ ገነን ሥርዐት በአማራ ወገኖቻችን ላይ የከፈተውን የህልውና ጦርነት ለአለም መንግስታት በማሳወቅ እና የአማራን ህዝብ ለነጻነት፣ለእኩልነት፣ ለለፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና አካታች ሐገራዊ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ፤ በጉልበትና በሀይል የተወሰዱ የአማራውን እርስት ለማስመለስ በሚደረገው የሰላማዊ ትግል መሳተፍና ማገዝ ወቅታዊ እና ቸል ሊባል የማይገባው መሆኑን ተረድተናል።  


በመሆኑም የአማራ ህዝብ ነጻነት በገጠመው የህልውና ፈተና ላይ የራሳችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት፤ መላው የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ከጎጥ ከፆታና ከሀይማኖት ልዩነት ሳይገድበው የአማራ ህዝብ በኢትዩጵያ ማህበራዊ፣ እኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለዘለቄታ መፍትሄ ለማምጣት እንዲያግዝና ከድህነት ለማላቀቅ በሚደረግ ጥረት ሁሉ እንዲተባበር በማመን፤  የሚመሰረተው የቤይ ኤርያ የአማራ ማህበር አሁን ኢትዮጵያን ከሚገዛው የብልፅግና ፓርቲ እንዲሁም ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ ተጽዕኖ የፀዳ፤  በሚታመኑ እውነተኛ የአማራ ተዋላጆች በሚመርጠው አመራር በሚያስቀምጠው ግብና በሚነድፈው ዕቅድ እንዲንቀሳቀስ አና እንዲመራ ፤ የቤይ ኤርያ የአማራ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግለት በማመን፣ የቤይ ኤርያ የአማራ ማህበር ሰኔ ፲, ፳፻፲፭ ዓ.ም. (June 17, 2023) በኦክላድ ከተማ፤ በካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት ተቋቋመ። 


የማህበሩ ራዕይ 


የአማራ ህዝብ የማህበራዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ የህልውና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት አስተማማኝ ድርጅት ሆኖ ማየት። 



የማህበሩ ተልዕኮ


1. በቤይ ኤርያ የሚኖሩትን የዐማራ ማኅበረሰብ ኅብረት እና አንድነት ማጠናከር፤

2. የዐማራን ሕዝብ ባህል በቤይ ኤርያ አካባቢ ማጎልበት እና ማስተዋወቅ፤

3. በቤይ ኤርያ አካባቢ የሚኖረውን የዐማራ ማኅበረሰብ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በሥራ መስክ እና በትምህርት ዘርፍ እርስ በእርስ የሚረዳዳበትን መርኃ ግብሮች መዘርጋት፤

4. የቤይ ኤርያ የዐማራ ማኅበረሰብ በአካባቢው ባለው የዐማራ ጉዳይ ትኩረት የሚሰጠው እንዲሆን እና ተሰሚነት እንዲያገኝ ተፅዕኖ መፍጠር ናቸው።


የማህበሩ አላማ





አድራሻችን፡ 


1319 Washington Avenue Unit 551, 

San Leandro, CA 94577 

amharabayarea@gmail.com

510-560-4215 




Join us